በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ ወገኖች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 416 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሣምንት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
እነዚህ ወገኖች ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በሳምንቱ ውስጥ በተደረጉ ዘጠኝ በረራዎች መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከተመለሱት መካከልም 2 ሺህ 859 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡
በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ መጋቢት 3 ቀን 2017 በይፋ መጀመሩን መረጃው አስታውሷል፡፡
ይህን ተከትሎም እስከ አሁን 3 ሺህ 416 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡