Fana: At a Speed of Life!

ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው እንጀራ ለገበያ ሲያቀርቡ የነበሩ 84 ግለሰቦች በቁጥጥ ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐዋሳ ከተማ አሥተዳደር ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው እንጀራ ጋግረው ለገበያ የሚያቀርቡ 84 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ እንደገለጹት፤ በዋናነት በታቦር፣ በቱላና ዳቶ ክፍለ ከተሞች ከዚህ ጋር በተያያዘ በ30 ቤቶች በተደረገ ፍተሻ ለጋገራ የተዘጋጀ ሊጥና ዱቄት ከተለያዩ ባዕድ ቁሶች ጋር ተይዟል፡፡

ግለሰቦቹ ፈቃድ ሳይሰጣቸው በማኅበር ራሳቸውን አደራጅተው ወደ ሥራ እንደገቡና ጤፍን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል በሕገ ወጥ መንገድ እንጀራ ጋግረው ለሆቴሎች ሲያቀርቡ እንደቆዩም ለኢዜአ ተናግረዋል።

የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ጥበቃና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ቡሪሶ ቡላሾ በበኩላቸው፤ ‎ከተያዙት ግብዓቶች ውስጥ ለምርመራ ከተላኩ 7 ናሙናዎች 5ቱ በሰው ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ንጥረ ነገሮቸ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.