Fana: At a Speed of Life!

ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጓጓዙ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የተገዙ ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች በተሸከርካሪ ተጭነው ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጓጓዙ ነው፡፡

አንደኛዋ ጀልባ “ጣና ነሽ – ሁለት” ስትሆን፤ ዘመናዊ መሆኗ እና ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የምትውል ናት ተብሏል፡፡

ጀልባዋ 38 ሜትር ርዝመት ሲኖራት፤ 188 ሰዎችን በአንድ ጊዜ የመጫን ዐቅም እንዳላት ተገልጿል፡፡

ሁለተኛዋ ጀልባ ደግሞ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ፣ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣና የመዝናኛ መሆኗን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡

ጀልባዎቹ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውኃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.