በክልሉ በ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚከናወነው የቢሮ ሕንጻ ግንባታ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የቦንጋ ብዝሃ ማዕከል የክልል ተቋማትና የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ ሕንጻ ግንባታን አስጀምረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት÷የሕንጻ ግንባታው የመንግስትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል መስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
ለግንባታው 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጀት መያዙን ገልጸው÷በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የቅርብ ክትትል ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
ለአካባቢው ሕብረተሰብ የሥራ ዕድል፣ የቴክኖሎጂና የዕወቀት ሽግግር ከመፍጠር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው መጠቆማቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡