Fana: At a Speed of Life!

ወደ እንግሊዙ ሄትሮው አውሮፕላን ማረፊያ የበረሩ አውሮፕላኖች አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተገደዱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለንደን በሚገኘው ሄትሮው አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በተነሳ የእሳት አደጋ ምክንያት አውሮፕላን ማረፊያው ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ ተሰምቷል፡፡

በአደጋው አውሮፕላን ማረፊያው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ያገጠመው መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎም በእንግሊዙ ሄትሮው አውሮፕላን ማረፊያ መዳረሻቸውን አድርገው ሲበሩ የነበሩ ከ120 በላይ አውሮፕላኖች አቅጣጫቸውን ቀይረው እንዲመለሱ መገደዳቸው ተመላክቷል፡፡

ሄትሮው አውሮፕላን ማረፊያ በዓለማችን በርካታ መንገደኞችን ከሚያስተናግዱ አውሮፕላን ማረፊያዎች መካከል አንዱ እንደመሆኑ በመንገደኞች ዘንድ ከፍተኛ መስተጓጎል ማስከተሉ ተጠቁሟል፡፡

አውሮፕላን ማረፊያው የተሳፋሪዎችን እና የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል እንደተዘጋ መገለጹን ሲኤንኤን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.