Fana: At a Speed of Life!

የደን ልማት የዘላቂ የምግብ ዋስትና መሠረት እንዲሆን እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 14ኛው የዓለም የደን ቀን “ደን እና ምግብ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፡፡

ባለፋት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ሥራዎች ሀገራዊ የደን ሽፋንን ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማድረስ መቻሉን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአከባበሩ ላይ ተናግረዋል፡፡

ይህን የደን ሽፋን እስከ 2030 ወደ 30 በመቶ ከፍ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የደን ልማት ዋና ዳይሬክተር  ከበደ ይማም በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ የደን ሀብት እንዲያድግ፣ የተራቆቱ እና አሲዳማ መሬቶች እንዲያገግሙ ትኩረት መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡

የደን ልማት የዘላቂ የምግብ ዋስትና መሰረት እንዲሆን የኢትዮጵያ የደን ልማት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

በጎህ ንጉሡ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.