Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፊንላንድ በውሃው ዘርፍ በሚያደርጉት ትብብር ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) በፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ፣ የመካለኛው ምስራቅና የላቲን ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሄሌና ኤራክሲነን ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት÷ የፊንላንድ መንግስትና ህዝብ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አድንቀው፤ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር የሚተገብረው አምስተኛው ዙር የኮዋሽ ፕሮግራም ሊያካሂዳቸው የሚገቡ ማሻሻያዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ውሃ አጠርና ድርቅ የሚያጠቃቸው አካባቢዎች፣ በግጭት ጉዳት የደረሰባቸው የመጠጥ ውሃ መሰረተልማቶች የሚገኙበት አካባቢዎች እና በጸሀይ ሃይል የሚሰራ የውሃ መሰረተ ልማት መገንባት ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አንስተዋል።

በተጨማሪም የውሃ አገልግሎቶችና የኮዋሽ ኮሚቴዎች የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ እና የውሃ ሀብት መረጃ ስርዓት ማዘመን ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት በሚያስችል መልኩ መተግበር እንደሚገባም ገልጸዋል።

በፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የመካለኛው ምስራቅና የላቲን ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሄሌና ኤራክሲነን አምስተኛውን ዙር የኮዋሽ ፕሮግራም አተገባበርን በተመለከተ በቀጣይ ውይይቶችን በማድረግ ውሳኔ ላይ እንደሚደረስ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.