የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለእስልምና እምነት ተከታዮች በአድዋ ድል መታሰቢያ ውስጥ የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ቡዜና አልካድር የእስልምና እምነት ተከታዮች እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት÷ የጾም ወቅት መተሳሰብ እና መረዳዳትን በማጎልበት አንድነታችንን ይበልጥ የምናጠናክርበት ነው።
ከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በየቀኑ በምገባ ማዕከላት የኢፍጣር መርሐ ግብር እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
በየዓመቱ በረመዳን ወቅት ከተማ አስተዳደሩ የኢፍጣር መርሐግብር ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ጋር እያካሄደ መሆኑንም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።