Fana: At a Speed of Life!

በሮቤ ከተማ በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሮቤ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው የደረሰው ከስናና ወረዳ ወደ ሮቤ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡

በተፈጠረው አደጋም የአምስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷23 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለጸው፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአቅራቢያ ከሚገኝ ሆስፒስታል ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑንና የአደጋው መንስዔ እየተጣራ እንደሚገኝ መጠቆሙንም የሮቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.