በዩክሬን የሰላም አስከባሪ ጦር ጉዳይ ከፍተኛ ወታደራዊ ስብሰባ ሊካሄድ ነው
በዩክሬን የሰላም አስከባሪ ጦር ጉዳይ ከፍተኛ ወታደራዊ ስብሰባ ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዩክሬን የሰላም አስከባሪ ጦር ጉዳይ ከ20 በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት ከፍተኛ ወታደራዊ ስብሰባ ዛሬ በብሪታንያ ይካሄዳል፡፡
በስብሰባው ላይ ብሪታንያና ፈረንሳይ በሚመሩት የሰላም ማስከበር ተልዕኮው ጥምረት የተካተቱ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን÷ በዕቅዱ አተገባበር ዙሪያ በዝግ ይመክራሉ ተብሏል፡፡
በስብሰባው ላይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እና የአውሮፓ ህብረት እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡
በምዕራባውያኑ ሀገራት የሚመራው በዩክሬን የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን የማሰማራት ዕቅድ ወደ ትግበራ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኬር ስታርመር ተናግረዋል፡፡
ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ወታደሮቻቸውን ወደ ዩክሬን ለመላክ ፍቃደኛ መሆናቸውንና ሌሎች የጥምረቱ ሀገራት በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡