Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ልዑክ ከልማት አጋሮች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ5ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የስራ ላይ ቡድን ስብሰባ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚገኘውና በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ልዑክ ከልማት አጋሮች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታከናውናቸው ሥራዎች ጋር በተያያዘ ድጋፍ በሚያስፈልጉን ጉዳዮች ላይ ከልማት አጋሮች ጋር ውጤታማ ውይይት እያደረግን እንገኛለን ብለዋል።

ውይይቱ በትናንትናው ዕለት ከተካሄደው የ5ኛው የሥራ ቡድን ድርድር የቀጠለ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ ላይ የዓለም ባንክ እና የአውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ ሕንድ፣ ቻይና፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፈንድ እና የዓለም አቀፉ የንግድ ማዕከል በሂደቱ አስፈላጊውን የፋይንናስና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውንም ገልጸዋል።

መድረኩ ከሰዓት በኋላም ቀጥሎ እንደሚካሄድ አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.