Fana: At a Speed of Life!

የሚተገበረው ስራ በተጨባጭ ውጤት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁሉም መስክ የሚተገበረው ስራ በተጨባጭ ውጤት ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ዱራሜ ክላስተር የሚገኙ የተለያዩ መስሪያ ቤቶችን አፈጻጸም በገመገምገም የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም በአፈጻጸም የተስተዋሉ ውስንነቶችን ማረም እና የተሻሉ ተግባራትን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸው÷ በሁሉም ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ስራን በውጤታማነት ለመምራት የድጋፍና ክትትል ስራ ማጠናከር መቻል በግብርና ሴክተር የተስተዋሉ መልካም ልምዶች ስለመሆናቸው አንስተዋል።

በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገር የሚያስችል ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅሰው÷ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን ከግብርና ስራ ጋር በማስተሳሰር የዜጎች የስራ ባህል እንዲሻሻል መስራት ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

ወጣቶች በልማት እና በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ውጤታማ መሆኑን ገልጸው፤ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ያላቸው ተሳትፎም አበረታች ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.