Fana: At a Speed of Life!

65 ኢትዮጵያውያን ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 65 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገሪቱ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ቢሮ ጋር በመተባባር ነው ኢትዮጵያውያኑ በአውሮፕላን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያደረገው፡፡

ሕገ-ወጥ የስደት መንገድ የሀገራትን መርሐ ከመጣሱ በላይ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት እየነጠቀ እንደሚገኝ ኤምባሲው አስታውቋል፡፡

ስለሆነም ዜጎች ራሳቸውን ለመሰል አደጋ በማጋለጥ የሚያደርጉት ሕገ-ወጥ ስደት ለመከላከል ባለድርሻ አካላት በትብበር እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.