Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት የላትም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ፍላጎት እንነጋገር፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ ህዝቦች በሚጠቀሙበት መርህ እንወያይ የሚል ነው ብለዋል።

የኤርትራ ህዝብ የሚያስፈልገው ልማት ነው፣ ተባብረን መልማትና መስራት እንጂ አንዱ አንዱን መውጋት የእኛ እቅድ አይደለም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ላይ ማንም ሀገር ወረራ ሊፈጽም እና ከጀመርነው ህልም ሊያስቆመን ይችላል የሚል ስጋት የለብንም ብለዋል፡፡

በቂ ዝግጅት ስላለን ማንም አያስቆመንም፣ ዝግጅት የምናደርገውም ጦርነትን ለማስቆም ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

የባህር በር ጥያቄን ማንሳት ነውርነቱ አቁሟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አቋምም በዓለም ላይ ትልቅ ሀገር ሆኖ የባህር በር የሌለው የለም ስለሆነም በሰጥቶ መቀበል መርህ ሊሆን ይገባል የሚል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ አጀንዳ ለመስጠት የመጣ ሳይሆን ባለፉት ዓመታት ትኩረት የተሰጠው እና በመደመር መጽሐፍ ላይ የተካተተም ነው ብለዋል፡፡

በብርሃኑ አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.