Fana: At a Speed of Life!

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና የኮሪደር ልማት ሥራን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ጎበኙ፡፡

ከርዕሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ በየደረጃው የሚገኙ የክልል እና የሀዲያ ዞን አመራሮች በጉብኝቱ ላይ መሳተፋቸውን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

አመራሮቹ በጉብኝታቸው በርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት አካባቢ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ መመልከታቸው ተገልጿል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በተገኙበት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ያለመ ውይይት ከዞን እና ከከተማው አመራሮች ጋር ከጉብኝቱ ቀደም ብሎ መካሄዱም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.