ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያ የንግድ ድርጅቶች ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር እንዲተባበሩ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገራቸው የንግድ ድርጅቶች ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በትብብር እንዲሠሩ አሳሰቡ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በሩሲያ የኢንዱስትሪ እና የሥራ ፈጣሪዎች ኅብረት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ተቋማቱ በብሪክስ አባል
ሀገራት ጋር በሚኖረው የንግድ እንቅስቃሴ በንቃት እንደሚሳተፉ ያላቸውን እምነት ጠቅሰዋል፡፡
የብሪክስ ሀገራት አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ ባለፈው ዓመት 4 ነጥብ 9 በመቶ ማደጉንም አውስተዋል፡፡
ለዚህም የሩሲያ የንግድ ድርጅቶች ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ሊሠሩ እንደሚገባ በአጽንኦት መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡
ሩሲያ ከብሪክስ ሀገራት ጋር በኃይል፣ ኢንዱስትሪ፣ ፋይናንስ እና መሰል ዘርፎች ያላት ትብብር እያደገ መምጣቱንም አረጋግጠዋል፡፡