Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትሃድ አየር መንገድ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትሃድ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት ትስስራቸውን ማጠናከር የሚያስችል ስምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

ስትራቴጂያዊ ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እና የኢትሃድ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶላዶ ኔቬስ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ለደንበኞች የተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ ለማቅረብ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና አቡዳቢ መካከል የበረራ አገልግሎት መጀመርን ያካተተ ነው ተብሏል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ እና የኢቲሃድ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሞሃመድ አሊ መገኘታቸውንም የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.