960 ተማሪዎችን የሚያስተናግደው አዳሪ ትምህርት ቤት በ243 ሚሊየን ብር ግንባታው እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአዳሪ ትምህርት ቤት ጎበኙ፡፡
ከ243 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ እየተገነባ ያለው ትምህርት ቤቱ፤ የመማሪያና የተማሪዎች ማደሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ ቤተ-መኩራ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ አይሲቲ ክፍልና ሌሎች መሠረታዊ ግንባታዎችን ማካተቱ ተገልጿል፡፡
ግንባታው ተጠናቅቆ በሙሉ ዐቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምርም ከ960 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይችላል መባሉን የጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡
በ2018 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምርም ይጠበቃል ተብሏል፡፡