Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሺ ዲባባ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአጭር እና በረጅም ርቀት እንዲሁም ጥሩነሺ ዲባባ የታዳጊዎች እና የአዋቂዎችን ውድድር በአንድ ጊዜ በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮናን በአጭር እና በረጅም ርቀት ያሸነፈው ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ሲሆን፤ በዚህም ለተከታታይ አራት ዓመታት በማሸነፍ ብቸኛው ሰው መሆን ችሏል፡፡

በሻምፒዮናው የአጭር ርቀት ውድድር ዘርፍ ከፈረንጆቹ 2006 ጀምሮ በመሰረዙ አትሌት ቀነኒሳ ቀደም ብሎ የጻፈው ደማቅ ታሪክ በማንም ሳይደገም ቀርቷል፡፡

አትሌቱ ከእነዚህ ውድድሮች በተጨማሪ በበርካታ ውድድሮች በተለያዩ የዓለም ሀገራት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ የቻለ ጀግና ነው፡፡

ሌላኛዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በተመሳሳይ ውድድር የታዳጊዎች እና የአዋቂዎችን በአንድ ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ያደረጋትን ታሪክ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ጽፋለች፡፡

አትሌቷ በወቅቱ የአዋቂ እና የታዳጊ ውድድርን ስታሸንፍ የ19 ዓመት ወጣት እንደነበረች ያስታወሰው የዓለም አትሌቲክስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.