Fana: At a Speed of Life!

በስፋት እየተከሰቱ ያሉ ማጭበርበሮች በምን መልኩ ሊፈጸሙ ይችላሉ?

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ የማጭበርበር ወንጀሎች ቁጥራቸው ክፍ እያለ መጥቷል።

ከማጭበርበር ጋር በተያያዘም ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርቶች ይቀርባሉ።

በመሆኑም ግለሰቦች የሚፈጸሙ ማጭበርበሮችን ለመከላከል በቅድሚያ በምን መልኩ ሊጭበረበሩ እንደሚችሉ ማወቅ ይገባል።

በዚህ ጽሑፍም አጭበርባሪዎች በምን መልኩ ወደ እኛ ቀርበው ሊያታልሉ የሚችሉበትን መንገድ እንጠቁማችኋለን፡-

  • በፍቅር ጓደኝነት ስም

አጭበርባሪዎች የፍቅር ግንኙነትን ወይም ጓደኝነትን እንደ ወጥመድ ይጠቀማሉ። እነዚህ ግንኙነቱ እውነት እንዲመስል ጠንክረው የሚሰሩ ሲሆን÷ የወጥመዳቸው ሰለባ የሆኑ አካላትን ከፍተኛ ገንዘብ ያጭበረብራሉ።

  • ትርፍ ለማግኘት ባለን ፍላጎት

ትርፍ ለማግኘት በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ አጭበርባሪዎች እኛን ለማማለል በቀላሉ ብዙ ገንዘብ የምናገኝበት አማራጭ እንዳላቸው በማስመሰል ሁሉንም አይነት የማጭበርበር ዘዴ በመጠቀም ገንዘባችንን ይወስዳሉ።

  • የምርት እና አገልግሎት አቅራቢ በመምሰል

አጭበርባሪዎች ምርቶችን እና አገልግሎቶችን የሚገዙ ወይም የሚሸጡ በመምሰል ሰዎችን በማጥመድ ያጭበረብራሉ።

  • በማስፈራራትና በዛቻ

አጭበርባሪዎች የእኛን ማንነት ወይም ገንዘብ ለማጭበርበር ማንኛውንም ታክቲክ የሚጠቀሙ ሲሆን÷ ግላዊ መረጃዎቻችንን መጥለፍና ከመለጠፍ እስከ የግድያ ዛቻ በማስፈራራት ሊያጭበረብሩን ይችላሉ።

  • በስራ ቅጥር ስም

ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሥራ እንደሚያስቀጥሩን በማግባባት ለቅጥሩ ቅድመ ክፍያ በመጠየቅ ገንዘባችንን አሳልፈን እንድንሰጣቸው በማድረግ ሊያጭበረብሩን ይችላሉ።

  • ድንገተኛ ሽልማት

አጭበርባሪዎች ያልቆረጥነውን ሎተሪ ወይም ያልተሳተፍንበትን ውድድር እንዳሸነፍንና ሽልማት እንዳገኘን በመንገር ሽልማቱን ለመውሰድ ቅድመ ክፍያ ወይም ሚስጥራዊ መረጃ እንድንሰጣቸው በማግባባት ያጭበረብራሉ።

  • ያልሆኑትን ሆኖ በመቅረብ

አጭበርባሪዎች እምነት የሚጣልበት ተቋም፣ የቅርብ ወዳጅ ወይም ቤተሰብ መስሎ በመቅረብ ገንዘብ የማጭበርበር ወይም መረጃ የመመንተፍ ድርጊት ይፈጽማሉ።

ምንጭ፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.