Fana: At a Speed of Life!

ከጌጣጌጥ ማዕድናት የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጌጣጌጥ ማዕድናትን መረጃ በማጥናትና በማዘመን ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር ገለጸ።

የማዕድን ሚኒስቴር እና የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኦፓል ማዕድን አቅርቦትና ግብይትን ቁልፍ ችግሮች ጥናት እና ዘመናዊ የገበያ ሞዴል ሰነድ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር በማዘጋጀት ለባለድርሻ አካላት አቅርቧል፡፡

በውይይት መድረኩ የማዕድን ሚኒስትር ዴኤታ ሚሊዮን ማቴዎስ እንዳሉት÷ በሀገሪቱ የሚገኙ የጌጣጌጥ ማዕድናትን መረጃ በሚገባ በማጥናትና በማዘመን የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በመድረኩ የኦፓል ማዕድን ሃብት እና አቅርቦት፣ በግብይት ላይ የሚታዩ ቁልፍ ችግሮች፣ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ እንዲሁም የኦፓል ማዕድን ገበያ አማራጭ ቀርቦ ውይይት መካሄዱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.