በ2ኛው የዓለም ጦርነት የብሪታኒያ አውሮፕላን አብራሪ የነበሩት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የብሪታኒያ ጦር አውሮፕላን አብራሪ የነበሩት ጆን ፓዲ ሄሚንግዌይ በ105 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
የዩናይትድ ኪንግደም ሮያል አየር ኃይል እንዳስታወቀው፤ ሄሚንግዌይ በፈረንጆቹ 1940 ብሪታኒያን ከናዚ ጥቃት ለመከላከል በተደረገው ጦርነት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ካበረከቱ ጥቂት አብራሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡
በወቅቱ ከነበሩት የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትርም አድናቆት እንደተቸራቸው አስታውሶ የዘገበው ታይምስ ነው፡፡
በጊዜው ከጀርመን አውሮፕላኖች ለሚሰነዘረው ጥቃት ምላሽ ከሚሰጡ ግንባር ቀደም አብራሪዎች መካከል እንደነበሩም ተገልጿል፡፡