Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ 27 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ዙር መስኖና በበልግ 103 ሺህ ሄክታር ማሳ በማልማት ወደ 27 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አስታወቀ።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) የተመራ ቡድን በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በአነስተኛ መስኖ በክላስተር የለሙ ማሣዎችን ተመልክቷል።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ተግባራት ሰፊ ለውጦች እየታዩ ነው።

በካፋ ዞን ጨና ወረዳ መስኖ ፕሮጀክቶች በ86 ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ እና የተለያዩ ፍራፍሬ እና አትክልቶች ላይ የሚሰሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው ብለዋል።

በሌሎች አካባቢዎችም ሰባት ዘመናዊ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታዎች ተገንብተው ወደ ሥራ መግባታቸውንም አክለዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ በበኩላቸው፤ በ2ኛ ዙር መስኖና በበልግ ወቅት 103 ሺህ ሄክታር ማሳ በማልማት ወደ 27 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የመስኖ አዉታሮችን ለማስፋት በተሰራዉ ሥራ ውጤት መመዝገቡን መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.