Fana: At a Speed of Life!

ሀሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን ለመለየት የሚያስችሉ ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማኅበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ከ4 እስከ 6 በመቶ የሚሆኑ አካውንቶች ሀሰተኛ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ።
በተለይ የቴክኖሎጂ እውቀት ለሌላቸው ሰዎች ሀሰተኛ አካውንቶችን ለመለየት ከባድ ሊሆን እንደሚችልም ይገለፃል።
አንድን የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንት ሀሰተኛ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለመለየት ፍንጭ የሚሰጡ አንዳንድ ምልክቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
1. ስለአካውንቱ ባለቤት ዝርዝር መረጃ አለመያዝ፣
2. ከጉግል ወይም ከሌሎች ድረ-ገጾች የተገኙ ፎቶዎችን መጠቀም፣
3. በብዛት ሌሎችን መከተል (follow) ማድረግና በአንጻሩ ጥቂት ሰው ይከተላቸዋል፣
4. ወጥነት የሌለው እንቅስቃሴ ማሳየት፣
5. በአብዛኛው አወዛጋቢ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች መለጠፍ፣
6. የወል ርዕስ ወይም ኦሪጅናል ያልሆነ ይዘትን መጠቀም፣
7. ግብስብስ መልዕክቶችን፣ አጠራጣሪ ሊንኮችንና ወጥ ያልሆነ ሃሽታጎችን ያጋራሉ፣
8. ለአንድ ርዕስ በጣም አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ይሆናሉ (ዋልታ-ረገጥነት)
ምንጭ፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.