Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በግንባታ ላይ ካሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል ሰባቱ ዘንድሮ ይጠናቀቃሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከለውጡ ወዲህ በሶማሌ ክልል ግንባታቸው ከተጀመሩ 18 የመስኖ ፕሮጀክቶች መካከል ሰባቱ አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን ተጨማሪ ሰባት ደግሞ ዘንድሮ እንደሚጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

በክልሉ እየተሠሩ ያሉ የመስኖ ልማት ሥራዎች በአርብቶ አደሩ ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸውን የክልሉ መስኖ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሞሐመድ ፈታህ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ያለውን የመልማት ዐቅም ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፤ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በክልሉ ያሉትን ወንዞች እና የከርሰ ምድር ውኃ በመስኖ ለመጠቀም ዕድል ሰጥቷል ነው ያሉት፡፡

ከለውጡ በፊት የነበሩት ከሦስት የማይበልጡ የመስኖ ፕሮጀክቶች አርብቶ አደሩን በሚፈለገው ልክ ተጠቃሚ አለማድረጋቸውን አውስተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከለውጡ ወዲህ 18 የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጀመሩን፤ ከዚህ ውስጥም ሰባቱ ተመርቀው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን እና ተጨማሪ ሰባት ደግሞ ዘንድሮ እንደሚመረቁ አመላክተዋል፡፡

መንግሥት የክልሉን አርብቶ አደር ኑሮ በማሻሻል ከፊል አርሶአደር እንዲሆን እና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.