Fana: At a Speed of Life!

የህልውና ጉዳይ የሆነው የወደብ አማራጭ ማስፋት ጥረት እንዲጠናከር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፍጥነት እያደገ የሚገኘውን የገቢና ወጪ ንግድ ለማሳለጥ የወደብ አማራጮችን ማስፋት የህልውና ጉዳይ መሆኑን የባለሀብቶችና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበራት ገለጹ።

አብዛኛው የሀገሪቱ የገቢና ወጪ ንግድ በጅቡቲ ወደብ ብቻ ጥገኛ በመሆኑ ዘርፉን ከማሳለጥ አኳያ ችግሮች መኖራቸውን ማኅበራቱ ጠቁመዋል፡፡

በዚህም አማራጭ ወደብ በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ ከዕቃ ማጓጓዝ ፍጥነትና ከዋጋ አንፃር ክፍተቶች እንዲፈጠሩ ማድረጉን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች እንደመሆኑ መንግሥት አማራጭ ወደቦችን ለማግኘት የጀመረው ጥረት ተገቢና ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸው፤ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ሀገሪቱ በተለያየ አቅጣጫ ወደብ ስታገኝ የወጪና ገቢ ንግዱን የበለጠ ለማሳለጥና ተወዳዳሪነትን ለማስፋት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የህልውና ጉዳይ የሆነው አማራጭ ወደብ የማስፋት ሥራ እንዲሳካ ባለሀብቶችና የሚመለከታቸው አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.