ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በሠመራ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ላይ፤ የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ ኢድሪስን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በጉብኝታቸውም፤ በሠመራ ከተማ እየተገነቡ የሚገኙትን የዳቦ እና የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች እንዲሁም የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴን መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ትናንት ምሽት የአፋርና የሶማሌ ሕዝቦችን አብሮነትና ትሥሥር ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ የጋራ ኢፍጣር መርሐ-ግብር በሠመራ ከተማ መካሄዱ ይታወቃል፡፡