የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ሰመራ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ገብተዋል፡፡
የአፋር እና ሶማሌ ወንድም ሕዝብ የጋራ ኢፍጣር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በሰመራ ከተማ ይካሄዳል፡፡
በመርሐ ግብሩ ለመታደምም አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የሰላም ሚኒስትር መሃመድ ኢድሪስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ሰመራ ገብተዋል።
አመራሮቹ ሰመራ ከተማ ሲገቡ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡