Fana: At a Speed of Life!

ንጋት ኮርፖሬት ለ9 ሺህ 494 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ንጋት ኮርፖሬት ውጤታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የኮርፖሬቱ የቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅትም ንጋት ኮርፖሬት ከትርፍ ባሻገር ኢኮኖሚውን የሚያግዙ በርካታ የኢንቨስትመንትና ማኅበራዊ ልማት ሥራዎች ማከናወኑ ተገልጿል።

ኮርፖሬቱ ለ9 ሺህ 494 ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን÷25 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ሃብት ማፍራቱም ተጠቅሷል፡፡

ንጋት ኮርፖሬት በፈረንጆቹ 2024 በጀት ዓመት 10 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ በመሰብሰብ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘት እንደቻለ መጠቆሙን አሚኮ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.