ኢትዮጵያና ጅቡቲ ሕገ-ወጥ ስደትን መቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰኢድ ኖህ ሀሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ሕገ-ወጥ ስደት መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡
በዚህም ኤምባሲው ከጅቡቲ ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እና በሕገ-ወጥ የደላሎች ሰንሰለት ላይ ተገቢውን ርምጃ ለመውሰድ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ዜጎች አስፈላጊውን የሕግ ከለላ እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ በሕጋዊ መንገድ የመጡ ዜጎች ላይ የሚያጋጥሙ የመብት ጥሰቶችን ለማረም በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡