Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሩሲያ-ዩክሬን የተኩስ አቁም ዙሪያ ከሩሲያ አቻቸው ጋር ይወያያሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ-ዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ዙሪያ በነገው ዕለት ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚወያዩ አስታወቁ፡፡

በዚህ ሳምንት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው፤ ስለተኩስ አቁሙ ጥረት ነገ አንድ ወሳኝ ዜና ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህን ያሉት ከሳንምት በፊት የዩክሬንና የአሜሪካ መልዕክተኞች በሳዑዲ አረቢያ ተሰብስበው ጦርነቱን ለማቆም ያስችላል ባሉት የ30 ቀናት የተኩስ አቁም ሃሳብ ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡

ነገ ይደረጋል የተባለው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የስልክ ውይይት በመሬትና የኃይል ማመንጫ ተቋማት ዙሪያ እንደሚሆን ትራምፕ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ስለግዛት የምናወራ ይመስለኛል፤ የግዛቱ ነገር እንደምታውቁት ከጦርነቱ በፊት ከነበረው በብዙ መልኩ የተለየ ይሆናል፤ ስለ ኃይል ማመንጫ ተቋማትም እንወያያለን፣ እሱ ዋናው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ለሶስት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ትናንት ማምሻውን ሁለቱም ሀገራት አንዱ በሌላው ላይ የድሮን ጥቃት ማካሄዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ለማስቆም ከዚህ በፊት ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ለ1 ሰዓት ከ30 ያህል በስልክ መምከራቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.