Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው አርቲስት መርዓዊ ስጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው መርዓዊ ሥጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ክላርኔት በመጫወት የሚታወቀው አርቲስት መርዓዊ፤ ከሙዚቀኛነቱ ባለፈ በትወና መድረክ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሏል፡፡

አርቲስት መርዓዊ ስጦት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ግንባር ቀደም ቦታ ከሚይዙ አንጋፋ ሙዚቀኞች መካከል አንዱ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

ከ55 ዓመታት በላይ በቆየበት የሙዚቃ ሕይዎቱ፤ በድምጻዊነት፣ በክላርኔትና አልቶ ሳክስ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችነት፣ በሙዚቃ ግጥምና ዜማ ደራሲነት እንዲሁም በአቀናባሪነት እና ሌሎች ተዘርፎች ማገልገሉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.