Fana: At a Speed of Life!

ለሕብረተሰቡ ጥያቄዎች የተሰጠው ምላሽ በዚህ ሣምንት እንደሚቀርብ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕብረተሰቡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ላቀረባቸው ጥያቄዎች የተሰጠው ምላሽና ማብራሪያ በዚህ ሣምንት እንደሚቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ባለፈው ሣምንት፤ በትምህርት፣ ጤና፣ ኢኮኖሚ ጉዳዮችና በሌሎች አምራች ዘርፎች ላይ ሕብረተሰቡ ጥያቄና ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን እንዲያቀርብ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሠረትም፤ ለቀረቡ ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን ጽሕፈት ቤቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ የሰጡትን ምላሽና ማብራሪያም በዚህ ሣምንት እንደሚያቀርብ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.