Fana: At a Speed of Life!

በባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 የባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ተስፋዬ ድሪባ በአንደኝት ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ርቀቱን ለመጨረስም 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ ፈጅቶበታል፡፡

በዚሁ ውድድር አትሌት ተስፋዬን በመከተል ኬንያውያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

ኢትዮጵያን የወከሉት አትሌት መኳንንት አየነው እና ካሳሁን ኃይሉ 6ኛ እና 10ኛ ደረጃ ይዘው ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት የብርጓል መለሰ 2 ሠዓት ከ20 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ በመግባት ውድድሯን ሁለተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

እንዲሁም አትሌት አይናለም ደስታ 4ኛ፣ ጎጃም ፀጋዬ 7ኛ፣ ዐይንአዲስ ተሾመ 9ኛ እና ዘርፌ ልመንህ 10ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.