የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
በውድድሩ አትሌት አብዙ ከበደ 2ኛ እንዲሁም መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።
የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን በቀዳሚነት ያጠናቀቀችው አትሌት ብሬነሽ ደሴ 50 ሺህ ብር ሽልማት ይበረከትላታል።
በ22ኛ ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር 16 ሺህ ተሳታፊዎች የተካፈሉ ሲሆን ከ150 በላይ አትሌቶች ጠንካራ ፉክክር አድርገውበታል።
በወርቅነህ ጋሻሁን