የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም በሊቨርፑል እና ኒውካስል ዩናይትድ መካከል ይደረጋል፡፡
ሊቨርፑል በግማሽ ፍፃሜው የሰሜን ለንደኑን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐርን አሸንፎ ለፍፃሜ መብቃቱ ይወሳል፡፡
እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ሌላኛውን የሰሜን ለንደን ክለብ አርሰናልን አሸንፎ ነው ለፍጻሜ የደረሰው፡፡
ዛሬ ለፍጻሜ የሚፋለሙት ሁለቱ ቡድኖች፤ በሁሉም ውድድር ባደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስበርስ ግንኙነቶች ሊቨርፑል በአራቱ ሲያሸንፍ በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።
በወንድማገኝ ፀጋዬ