Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በጅግጅጋ ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በጅግጅጋ ገርባሳ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተው ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞችን ጎብኝተዋል።

በስልጠና ላይ የሚገኙት 25ኛ ዙር ምልምል የፖሊስ ሰልጣኞቹ በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ ማንኛውንም የፀጥታ ችግሮችን መመከት የሚችሉና የሚሰጣቸውን ግዳጅ ሁሉ በብቃት እንደሚፈጽሙ ባሳዩት የተግባር ልምምድ አረጋግጠዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ የሶማሌ ክልል መንግስት በጅግጅጋ ከተማ እያስገነባ ያለውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ሆስፒታልንም መጎብኘታቸውንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.