የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ሺህ 446ኛውን የረመዷን ፆም ምክንያት በማድረግ ታላቅ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ማካሄዱን አስታውቋል፡፡
መርሐ-ግብሩ የተካሄደው ”አብሮነት ለበጎነት፤ በረመዷን” በሚል መሪ ሐሳብ በስካይ ላይት ሆቴል መሆኑን የባንኩ መረጃ አመላክቷል፡፡
የሐይማኖት አባቶችን ጨምሮ የሲቢኢ ኑር የሸሪዓ አማካሪ ምክር ቤት አባላት፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመርሐ-ግብሩ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡