Fana: At a Speed of Life!

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ ነገ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እና የኮሚሽነሮች ይፋዊ የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት መሃመድ አሊ ዩሱፍ ከተሰናባቹ ሙሳ ፋኪ ማሀማት ስልጣን በመረከብ በይፋ ስራ ይጀምራሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.