Fana: At a Speed of Life!

ሚድሮክ በ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለሚገነባው ቅንጡ ሪዞርት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

 

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሐዋሳ ለሚገነባው ቅንጡ ሪዞርት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

‘ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ሐዋሳ’ የሚል ስያሜ ያለው ሪዞርቱ በ21 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን÷ እስከ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግበት ተገልጿል።

የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን የሚያቀርበውን ሪዞርት በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ መታቀዱ ነው የተገለጸው፡፡

ቅንጡ ሪዞርቱ ትልልቅ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን በብቃት የማስተናድ አቅም ኖሮት የሚገነባ ሲሆን÷ለሆቴል እና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ሪዞርቱ በግንባታ ሒደት ለ500 ሰዎች እንዲሁም ተጠናቅቆ ወደ ስራ ሲገባ ከ350 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.