Fana: At a Speed of Life!

የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ እስኪጠናቀቅ የትራንስፖርት ተርሚናሎች ዝውውር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎችን ተከትሎ የትራንስፖርት ተርሚናሎች ዝውውር መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በዚህም ከነገ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ:-

1. አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ፤

2. ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል፤

3. በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር የተዘዋወሩ ሲሆን ÷ስብሰባዎቹ እንደተጠናቀቁ ወደ ቀድሞ ቦታዎቻቸው እንደሚመለሱ ተገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ ተርሚናሎቹ ወደ ነበሩበት እስኪመለሱ ድረስ የከተማዋ ነዋሪዎች ለሚያሳዩት ትእግስትና ትብብር ምስጋና አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.