Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ቴሌኮም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ መሙያ ማዕከላትን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ መሙያ ማዕከላትን በዛሬው ዕለት ሥራ አስጀምሯል፡፡

ባትሪ መሙያዎቹ አልትራ ፋስት፣ ሱፐር ፋስትና ድንገተኛ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጀር የተሰኙ መሆናቸውን የኢትዮ ቴሌኮም ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡

ከቦሌ-መገናኛ ባለው መንገድ የተገነቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ መሙያ ማዕከላት ሥራ የጀመሩ ሲሆን ፥ ይህም የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ አንድ አካል ነው ተብሏል፡፡

ማዕከላቱ በደቂቃዎች የተሽከርካሪ ባትሪዎችን በመሙላት የሰውን ልጅ ሕይወት እንደሚያቀሉ ታምኖባቸዋል ተብሏል፡፡

ለሦስት ወራት የሚቆይ በ10 ብር አንድ ኪሎ ሜትር የሚያስኬድ ሃይል እንደሚሞላ የተገለጸ ሲሆን ፥ በአንድ ጊዜ የ32 መኪናዎችን ሃይል መሙላት የሚያስችል ባትሪ በመሙያ ማዕከላቱ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

በተያያዘ ዜናም ኢትዮ-ቴሌኮም 130 ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሁለት ዘመናዊ መኪናዎችን ለባለ እድለኛ ተሸላሚዎች አስረክቧል፡፡

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.