Fana: At a Speed of Life!

የአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል እና ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ዋና ዳይሬክተሯ፥ ቀደም ብሎ ከገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።

ከሰዓት በኋላም ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከልን እና ብርሃን የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

ክሪስታሊና በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሁለት ቀናት ቆይታ፥ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ፖሊሲዎች እና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከግሉ ዘርፍ ተዋንያን ጋር በኢትዮጵያ ስላሉ የንግድ እና ኢኮኖሚ እድሎች ሃሳቦችን እንደሚለዋወጡ መጠቆሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዋና ዳይሬክተሯ ጉብኝት አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያ ለማይበገር እና ዘላቂነት ያለው ጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገት ለምታደርገው ጥረት ያለውን የድጋፍ ቁርጠኝነት የሚያመላክት እንደሆነም ነው የተመላከተው።

ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምን በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.