በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለተሳተፉ የእህት ፓርቲዎች ተወካዮች ምስጋና ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለተሳተፉ የወዳጅ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ተወካዮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተሳተፉ የሚገኙ የወዳጅ ሀገራት እህት ፓርቲ ተወካዮች የብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሙዚዬምን ጎብኝተዋል፡፡
በመቀጠልም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ እና አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተገኙበት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡
ወ/ሮ አለምጸሃይ በዚህ ወቅት÷በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለተሳተፉ የወዳጅ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ተወካዮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተወካዮቹ በኢትዮጵያ እየተገነቡ የሚገኙ እና የተገነቡ የቱሪስት መዳረሻዎችን ተዘዋውረው በመጎብኝታቸውም አመስግነዋል፡፡
በቀጣይ በኢትዮጵያ የተመለከቱትን የቱሪስት መዳረሻ በሀገራቸው እንዲያስተዋውቁ እና በድጋሚ እንዲጎበኙም ጋብዘዋል፡፡