Fana: At a Speed of Life!

አየር ኃይል ለገነባው ከፍተኛ ወታደራዊ የዝግጁነት አቅም የሙያተኛው ሚና ጉልህ ነው – ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አየር ኃይል አሁን ለገነባው ከፍተኛ ወታደራዊ የዝግጁነት አቅም የሙያተኛው ድርሻ ጉልህ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ገለጹ።

የኢፌዲሪ አየር ሃይል ሎጂስቲክስ የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር በአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ ተካሂዷል፡፡

ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የአየር ኃይል ሎጀስቲክስ የተቋሙን የማድረግ አቅም ወደ ላቀ ከፍታ ያሸጋገሩ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

አየር ኃይሉ ለገነባው አሁናዊ ከፍተኛ የዝግጁነት አቅም የክፍሉ ሙያተኞች ድርሻ ከፍተኛ ሚና እንደነበረውም ነው የገለጹት፡፡

ተቋሙ አዳዲስ የአቪዬሽን ትጥቆችን ከመታጠቅ ባለፈ ያሉትን ጠግኖ ወደ ግዳጅ በማሰማራት ረገድ ክፍሉ ያከናወነው ተግባር የሚደነቅ እንደሆነ መጠቀሱን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ለተቋሙ የግዳጅ አፈፃፀም ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ክፍሎች የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፍኬት አበርክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.