የዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ላዕላይ ም/ቤት አባል አንድሬይ ክሊሞቭ በብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ ያደረጉት ንግግር …
የሩሲያን ገዥ ፓርቲ የዩናይትድ ራሺያ ፕሬዚዳንት፣ የሩሲያ ፌደሬሽን የጸጥታ ም/ቤት ምክትል ሃላፊ ድሚትሪ ሜድቬዴቭን ደብዳቤ (መልዕክት) ሳቀርብላችሁ ከፍ ያለ ክብርና ኩራት ይሰማኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔን በማስመልከት ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ልገልጽልዎ እዎዳለሁ።
በዚህ ጉባዔ በሚኖረው ውይይት ለኢትዮጵያ መጻኢ ዕድገት ፈጣንና ጠንካራ መሰረት እንደሚጥል እና በዓለም አቀፍ መድረክ የሚኖራትን ሚና እንደሚያጠናክርላት ዕምነቴ ነው።
በረጅም ዓመታት ጠንካራ ወዳጅነት የተገመደና በአስተማማኝ መሰረት ላይ የተገነባ የፖለቲካ፣ የንግድ እና የሌሎች ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብር እንዲሁም እንደ ብሪክስ እና ሩሲያ አፍሪካ የትብብር ፎረም ባሉ በባለ ብዙ ወገን መድረኮች የጋራ ተጠቃሚነትን እና ትብብራችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እርግጠኛ ነኝ።
ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ በፈረንጆቹ የካቲት 3 ቀን 2021 ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በተፈራረሙት የግንኙነትና ትብብር መንፈስ መሰረት ግንኙነታቸው እንዲጠናከር ቀጣይነት ባለው መንገድ ጥረት ያደርጋል።
በሀገሮች ነፃነት ንቅናቄ ማዕቀፍ ውስጥ ያለውን የኒዮኮሎኒያሊዝም ዘመናዊ ስርዓት መዋጋትን ጨምሮ በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ለማድረግ ሁሌም ዝግጁ ነን፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለመላው የጉባዔ ተሳታፊዎች ውጤታማ ሥራ እና ቀጣይ ስኬት፣ ሰላምና ብልጽግና ለኢትዮጵያ እንዲሆን እመኛለሁ!
ከአክብሮት ጋር፣ ድሚትሪ ሜድቬዴቭ
ፈቃዳችሁ ከሆነ በግሌ ጥቂት ነገር እንድናገር ፍቀዱልኝ…
ልክ የዛሬ 4 ዓመት ከጓደኞቼ ጋር እዚህ ሆኜ ይህንን ስምምነት ፈርሜያለሁ። በእነዚህ 4 ዓመታት ውስጥ እድገታችሁ የሚታይ እና የላቀ መሆኑን ለመመስከር እሻለሁ።
በትክክለኛው መንገድ ላይ ናችሁ።
መልካም ዕድል ለብልጽግና፣
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፣