የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ይገኛል።
ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሀሳብ ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል።
የፓርቲው መደበኛ ጉባኤ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜው በጉባኤው አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ ሪፖርት እና በሁለተኛው ጉባኤ የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።
ጉባኤው በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ኮሚቴው በቀረበ ሪፖርት ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን÷ ሪፖርቱን በውይይት አዳብሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በቀጣይ መርሐ ግብሩም በቀሪ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም እንደሚያስቀምጥ የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡