ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመሃንዲስ ዋና መምሪያ እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ፊልድ ማርሻሉ በመሃንዲስ ዋና መምሪያው የተገነባውን ዘመናዊ የብሎኬት እና የቴራዞ ማምረቻ ፋብሪካን ተመልክተዋል።
ፋብሪካው 20 ሺህ ብሎኬት በቀን ማምረት እንደሚችል እና በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመሃንዲስ ዋና መምሪያ ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር የሚያከናውናቸው ስራዎችንም ጎብኝተዋል።
በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ እየተገነባ የሚገኘው የባህር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ የህንፃ ግንባታ ሂደትን ሲጎበኙ በመሃንዲስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
በምልከታውም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለቀጣይ ሥራ ይበልጥ ሊያግዙ የሚችሉ ሃሳብ እና አሥተያየቶች መስጠታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።