ብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄደው የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶችና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ታድመዋል።
በተጨማሪም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ተገኝተዋል።
ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው የፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎች እና ወሳኝ አቅጣጫዎችም የሚተላለፍበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።