የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋሽንግተን ዲሲ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋሽንግተን ዲሲ የተከሰተው የአውሮፕላንና ሄሊኮፕተር መጋጨት አደጋ የሰዎችን ህይዎት በመንጠቁ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡
እንደ አሜሪካ አቪዬሽን አስተዳደር መረጃ÷ አውሮፕላኑ 60 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን ፥ ሄሊኮፕተሩ ደግሞ ሦስት ወታደሮችን ጭኖ ነበር፡፡
የአውሮፕላን አደጋው የደረሰው ፖቶማክ የተባለ ወንዝ አቅራቢያ መሆኑም የሚታወቅ ሲሆን፥ እስካሁን በርካቶች ለህልፈት ተዳርገዋል ተብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመልዕክቱ ጸሎታችንና ሃሳባችን ከተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ጋር ነውም ብሏል፡፡